በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"አቦል ደሞዜ" የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት ተጀመረ


"አቦል ደሞዜ" የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት ተጀመረ
"አቦል ደሞዜ" የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት ተጀመረ

ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓም ቡና ባንክ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ "አቦል ደሞዜ" የተባለ የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል።

በሙከራ አገልግሎት ላይ የቆየ መኾኑ የተገለጸው "አቦል ደሞዜ" ለተቀጣሪ ደመወዝተኛ የኅብረተሰብ ክፍል አገልግሎት እንዲሰጥ የተዘጋጀ መተግበሪያ መሆኑን የካቻ ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት እና የቡና ባንክ ኃላፊዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

"አቦል ደሞዜ" የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:14 0:00

ሠራተኞች ከደመወዝ ክፍያ ቀናቸው ቀደም ብሎ የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ከወር ደሞዛቸው የተወሰነውን ክፍል ያለምንም ማስያዣ በብድር እንዲያገኙ ያስቻላቸው መኾኑን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ነዋሪዎቹ ወ/ሮ ሶስና እና አቶ እስራኤል በቀለ ገልጸውልናል።

በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ያሉት መተግበሪያ ከኑሮ ውድነት አንጻር ገቢያቸውን ከወር እስከ ወር ማብቃቃት ለተቸገሩ ተጠቃሚዎች መፍትሄ መሆኑንም ከኢት ፊን ቴክ ተቋም የሂሳብ አያያዝ ባለሞያና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካሪ አቶ በረከት ቦጋለ አብራርተዋል፡፡

ከብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ሰጭነት ፈቃድ ማግኘታቸውንና በባንኩ የዘወትር ቁጥጥር የሚደረግበት መሆኑን የካቻ ማርኬቲንግ የግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ ናሆም አበራ ገልጸዋል፡፡

አቶ ናሆም አክለውም የዚህ አዲስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የደመወዛቸውን 33 ወይም 50 በመቶ በቀላሉ ካሉበት ሆነው በካቻ የሞባይል መተግበሪያ ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።

ከመንግሥታዊው ቴሌብር እና ከኬኒያው ሳፋሪኮም ኤም -ፔሳ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ውስጥ የግል ድርጅቶች የተጀመረው አገልግሎት መሆኑን ያነጋገርናቸው ባለሞያና የድርጅቶቹ ኃላፊዎች ገልጸውልናል።

ሠራተኞች አገልግሎቱን ለማግኘት የቡና ባንክ ወይም የካቻ ደንበኞች መሆን እንደሚጠበቅባቸው አገልግሎቱን ያበለፀገው ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ጥላሁን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

አገልግሎቱን ለመጠቀም የስልክ ባለቤትነትን የሚጠይቅ መሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የስልክ ተጠቃሚዎች ቁጥር አነስተኛ መሆንና ከኢንተርኔት መሠረተ ልማት ውስንነት እንዲሁም ተደራሽነቱን ከማስፋት አንጻር ገና ብዙ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG