በኢትዮጵያ በሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ዋነኛ ተጎጅዎቹ ወጣቶች መኾናቸው የሚደርሰውን ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ከፍ እንዲል አድርጎታል ሲሉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
ለችግሩ ዘላቂ መፍተሔ ለማምጣትም መንግሥት በትኩረት እንዲሠራ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገድ ደኅንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት በበኩሉ የትራፊክ አደጋ አሁንም ሀገራዊ ስጋት መሆኑን ጠቅሶ የተጎጅዎች መጠን ግን እየቀነሰ መምጣቱን አስታውቋል፡፡
የመንገድ ደኅንነትነትን በትምህርት ስርዐት ውስጥ እንዲካተትና የሕግ ማሻሽያዎችን በማድረግ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እየሠራሁ ነው ብሏል፡፡ ዝርዝር ዘገባው ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም