በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ሆኑ


ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ
ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መሾሙን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መሾሙን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በሞት ከተለዩ በኋላ ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን ላለፉት ሁለት ወራት በጊዚያዊነት የግድቡን ግንባታ ሲመሩት ቆይተዋል፡፡

ዛሬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዶ/ር አብርሃም በላይ ለግድቡ ግንባታ ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች ሹመት መስጠታቸውን የዜናው አገልግሎት ጠቁሟል።

በዚህም መሰረት ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ሥራ አስኪያጅ፣ ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳንና አቶ ፍቃዱ ከበደ ደግሞ ምክትል ሥራ አስኪያጆች ሆነው ሥራውን እንዲመሩ መመደባቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ማስታወቁን የኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት ገልጿል።

በራሳችን ሃገራዊ አቅም ያጋመስነው የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ለስኬት እንዲበቃ መላው ህዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG