ዋሽንግተን —
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች፣ ቃሊቲ፣ ዝዋይ ድሬዳዋና ሸዋ ሮቢት እንዲሁም የፌደራል ማረሚያ ቤቶችን ሥራ በውክልና ከሚያከናውኑ ከደቡብና ከትግራይ ክልሎች እንዲሁም ሀረር ከሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ይቅርታ እንዲደረግላቸው ለይቅርታ ቦርድ ከቀረቡ 755 ታራሚዎች መካከል 720ዎቹ መሥፈርቱን በማሟላታቸው መፈታታቸውን መንግሥት አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከነበሩት መካከል ሦስቱ የተፈቱት ከአራት ዓመታት እሥራት በኋላ ነው፡፡
ሌሎች የኮሚቴው አባላትና ኮሚቴው እንዲፈቱ ሲጠይቁ የነበሩ ደጋፊዎቻቸው አሁንም በእስር እንደሚገኙ ይናገራሉ።
ከእስር ከተፈቱት መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መካከል የኮሚቴውን የሕግ ተጠሪ ኡስታዝ ከሚል ሸምሱን ጋር የተካሄደ ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።