በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ገለፁ


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ “የዴሞክራሲያዊ ምኅዳሩን ለሁሉም ሰፊ ለማድረግ” ባሉት ጥረቶች ምክንያት፣ የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ “የዴሞክራሲያዊ ምኅዳሩን ለሁሉም ሰፊ ለማድረግ” ባሉት ጥረቶች ምክንያት፣ የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ፣ ተቃዋሚዎችን በማፈንና በማዕከላዊ እሥር ቤት በማስገባት ማሰቃየትን ጨምሮ፣ በሰብዓዊ መብቶች ረገጣ እንደምትከሰስ ይታወቃል።

መንግሥት ዛሬ በሰጠው በዚህ ያልተጠበቀ መግለጫ አቶ ኃይለማራም እንደተናገሩት፣ ቀደም ሲል ወንጀለኞች ተብለው ፍርድ በመጠባበቅ ላይ የነበሩ እሥረኞች፣ ክሳቸው፣ ውድቅ ይሆናል።

"ማዕከላዊ" የተባለው ዘግናኙ የአዲስ አበባው እሥር ቤት ወደ ሙዚየም እንደሚለወጥ የተናገሩት አቶ ኃይለማራም፣ ክስ የሚጠብቃቸውና ቀድሞውንም ወኅኒ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞ እንደሚፈቱም ገልፀዋል።

የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው ሂዩማን ራይትስ ዋች “እስረኞች ላይ ህገ ወጥ ምርመራ፣ ሰቆቃም ጭምር ይፈፀምበታል” ሲል እአአ በ2013 ገልጿል፡፡

ማዕከላዊ፣ ስንት እስረኞች እንዲሚገኙ ግልፅ አይደለም።

ማዕከላዊ
ማዕከላዊ

ሂዩማን ራይትስ ዋችም ሆነ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያውን መንግሥት በጅምላ እሥራት፣ ታሳሪዎች ላይ ሰቆቃ በመፈፀምና በፖለቲካ እስረኞች ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ ይዞታ በመፈፀም ይከሱታል።

የአቶ ኃይለማርያም መግለጫ ይፋ የሆነው ከቅርብ ወራት ወዲህ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የተካሄዱትን አያሌ ፀረ መንግሥት ተቃውሞዎች ተከትሎ መሆኑን ያጤኗል።

ተቃውሞዎቹ በመላ ሀገሪቱ በመዛመታቸው፣ መንግሥቱ በተቃውሞዎቹ ምክንያት እንዲያነሳ የተገደደውንና ለአንድ ወር የዘለቀውን የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ማውጣቱም አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG