ካሌ ከምትባለው የፈረንሳይ ሰሜናዊ ወደብ አቅራቢያ ከሚገኘውና “The Jungle” ወይም ጫካው ተብሎ በሚጠራው የስደተኞች መጠለያ መንደር ውስጥ እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞች እንደነበሩ ከእነዚህም ውስጥ ወደ 2ሺሕ የሚጠጉት ከ18 ዓመት በታች መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን የስደተኞች ዝውውር ታዛቢ ገለጹ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አጥኚ በተለይ በዚች የፈረንሳይ ሰሜናዊ ወደብ አቅራቢያ ካሌ በተባለች ቦታ የሚገኘው “ጫካው” የተባለው የስደተኞች መንደር ስደተኞች የምዝገባና መልሶ ማስፈር ሂደት ታዛቢ የሆኑት አቶ ካሊድ አብዱ ለአሜሪካ ድምጽ ለትግረኛ ቋንቋ አገልግሎት በሰጡት ቃለ ምልልስ በስደተኞቹ መንደር ከሚገኙት ስደተኞች መካከል 20 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያ እና ኤርትራውያን እንደሆኑ ገልጸዋል። ስደተኞቹ ፈረንሳይ ውስጥ ወደሚገኙ ወደ ተለያዩ 480 ስደተኛ ካምፖች እየተዘዋወሩ እንደሚገኙ ታውቋል።
በአሁኑ ሰዓት ወደ ሌላ ቦታ እየተወሰዱ ከሚገኙት መካከልም ጽዮን ግርማ የተወሰኑትን አነጋገራ ተከታዩን ዘግባለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።