በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል በአፋጣኙ ርብርብ ውስጥ


የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በደቡብ ኢትዮጵያ በድርቅ ጉዳት ከደረሰባቸው ወገኖች መካከል 165 ሺህ የሚሆኑትን የመርዳት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ።

እርዳታውን የሚሰበስበውም የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት መሆኑን ገልጿል።

የእርዳታው እንቅስቃሴ መሠረት ያደረገውም መንግሥታ ያወጣውን ሠነድ መሆኑን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

ከሐምሌ ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የአደጋ መከላከል፣ ዝግጁነትና ዋስትና ዘርፍ ባለፈው ወር ይፋ ማድረጉ ይታወሣል፡፡

መሥሪያ ቤታቸው ይህንኑ መንግሥት ያወጣውን ሠነድ መሠረት አድርጎ በደቡብና በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ድርቁ ያስከተለውን ጉዳት በባለሙያዎች አስቃኝቶ ክፍተት እንዳለ መረዳቱን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ወርቁ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ማኅበሩ በዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ቅኝት ተመሥርቶ ለሚሠጠው እርዳታ ከአሥር ሚሊየን በላይ የስዊስ ፍራንክ ለማሰባሰብ የውጭ ለጋሾችን ችሮታ ጠይቆ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሚሊየን በላይ የስዊስ ፍራንክ መሰብሰቡን ምክትል ዋና ፀሐፊው ዶ/ር የሺጥላ ኃይሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG