በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሥራ አጥነት እጅግ አሳሳቢ ብሔራዊ ችግር እንደኾነ መንግሥት ገለጸ


ሥራ አጥነት እጅግ አሳሳቢ ብሔራዊ ችግር እንደኾነ መንግሥት ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:44 0:00

ሥራ አጥነት እጅግ አሳሳቢ ብሔራዊ ችግር እንደኾነ መንግሥት ገለጸ

በኢትዮጵያ፣ ሥራ አጥነት እጅግ አሳሳቢ ብሔራዊ ችግር ከኾነበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ንጉሡ ጥላሁን፣ በዐዲስ አበባ የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የሥራ ዐውደ ርእይ ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር፣ ሥራ አጥነት የችግሮች ሁሉ አውራ እንደኾነ ገልጸው፣ ኹሉም ባለድርሻ አካላት ለመፍትሔው እንዲተጉ ጠይቀዋል፡፡

ትላንት ረቡዕ የተከፈተው ዐውደ ርእዩ፣ ከ20ሺሕ በላይ ዐዲስ ተመራቂ ሥራ ፈላጊዎችንና 200 ቀጣሪ ድርጅቶችን ያገናኛል፤ ተብሏል፡፡ ልዩ ልዩ አካላት በትብብር እንዳዘጋጁት የተነገረለት ይኸው ሀገር አቀፍ የሥራ ዐውደ ርእይ፣ ለስድስት ሺሕ ዐዲስ ተመራቂዎች፣ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተመልክቷል፡፡ በዝግጅቱ የተሳተፈው ዳሽን ባንክ፣ በሁለት ቀኑ የሥራ ዐውደ ርእይ፣ ሦስት ሺሕ ዐዲስ ምሩቃንን እንደሚቀጥር አስታውቋል፡፡

ዐውደ ርእዩ፣ ተቀጣሪዎችንና ቀጣሪዎችን በማገናኘት መልካም ዕድል እንደፈጠረ፣ የኹነቱ ተሳታፊዎች እና ሥራ ፈላጊዎች ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG