በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቦረና ዞን ሶዳ ቀበሌ ዛሬ አራት ሰው ተገደለ


በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ውስጥ በምትገኘው ሜጋ ከተማ አቅራቢያ በነዋሪዎችና በመከላከያ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች መገደላቸውና 18 መቁሰላቸው ተገለፀ።

በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ውስጥ በምትገኘው ሜጋ ከተማ አቅራቢያ በነዋሪዎችና በመከላከያ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች መገደላቸውና 18 መቁሰላቸው ተገለፀ።

በሌላ በኩል ደግሞ በኦሮምያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ በምትገኘው ወሊሶ ከተማ ውስጥም የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱና ሌሎችም ጥያቄዎችን የያዙ የከተማዪቱና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ሰልፍ መውጣታቸው ታውቋል።

ትናንት ሻሸመኔ ከተማ ውስጥና በሌሎችም የተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ውስጥ ሰልፎች ሲደረጉ በፀጥታና በፌደራል ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች ስድስት ሰው መገደሉን የክልሉ ቃል አቀባይ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮምያ ገዥ ፓርቲ የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - ኦህዴድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች በተካሄዱ ሰልፎች ለጠፋው የሰው ሕይወትና ለደረሰው የአካል መጉደል ኀዘን እንደተሰማው አስታውቋል።

ሻሸመኔና ምዕራብ ሃረርጌ ዞን ውስጥ ጉዳት ያደረሱ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኦሕዴድ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር አብይ አህመድ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በቦረና ዞን ሶዳ ቀበሌ ዛሬ አራት ሰው ተገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:53 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG