አዲስ አበባ —
"ወንጀለኞች ገና ከየጎሪያቸው ይወጣሉ" ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ይሄን ያስታወቁት በሌብነትና በሰብዓዊ ጥሰት ተጠርጥረው እየተያዙ ያሉ ስዎችን አስመልክተው ባወጡት መግለጫ ነው፡፡ ወንጀለኞቹን የማደኑና በሕግ የመቅረቡ ሂደት ገና ይቀጥላል ተጀመረ እንጂ አልተፈፀመም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በተጠርጣሪዎቹ የተፈፀመውን ወንጀል "ካንሰር" ሲሉ የገለፁት ጠ/ሚኒስትሩ ሁላችንም ልንከላከለው የሚገባ ነው በማለት አሳስበዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ