ዋሽንግተን ዲሲ —
በአስተሳሰብና በአመለካከት ልዩነታቸው ብቻ በአሸባሪነት ተፈርጀው በእስር ላይ የሚገኙ እስረኞችን ለማሰብ በትናንትናው ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተደረገው የአንድ ቀን ዘመቻ የተሳካ እንደነበር አስተባባሪዎቹ ገልፀዋ።
“እስረኞችን ለማስታወስ በተካሄደው የኢንተርኔት ላይ ዘመቻ የተነሱት ታሪኮች የኔም ልጅ ታሪክ ነው” ያሉን ደግሞ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበረ ልጃቸው እስር ቤት ውስጥ ተደብድቦ መሞቱን የገለጹ አባት ናቸው።
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አባዲ በእስር ቤቶችና በፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የተደረገው የክትትል ሪፖርት በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ