ዋሽንግተን ዲሲ —
ዋሽንግትተ ፖስት ጋዜጣ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርመለስ ዜናዊ ህልፈት አንደኛ አመትን ለማሰብ ስለተደረገው ስነስርአት ባወጣው የአሶሼተድ ፕረስ ዘገባ አቶ መለስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ አንድ አመት ቢያልፍም የተለወጠ ነገ የለም ይላል።
ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አመቱን ሙሉ ሲሞገሱ ቆይተዋል። ምስላቸውም በሀገሪቱ ዙርያ በሚገኙት የመንግስት መስርያ ቤቶች እንደተሰቀለ ነው ይላል ጋዜጣው ላይ የወጣው ዘገባ።
በሀገሪቱ ዙርያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርአት ተደርጎላቸዋል። ለሳቸው ማስታውሻም ከአርባ ስምንት በላይ የመናፈሻ ቦታዎች ተመስርተዋል። በመዲናይቱ አዲስ አበባም የሳቸው ስራዎች የሚዘከሩበት ቤተ መዘክር ለመገንባት መሰረተ-ዲንጋይ ተጥሏል።
የሱዳንና የሶማልያ ፕረዚዳንቶችን የመሳሰሉት በዝክረ መለስ ስነ-ስርአት
የተገኙት የአፍሪቃ መሪዎች “የአፍሪቃ ድምጽ” በማለት አቶ መለስን እንዳሞገሱ ዋሽንግትተ ፖስት ጋዜጣ ላይ የወጣው የአሶሼትድ ፕረስ የዜና አገግሎት ዘገባ ጠቅሷል። ሌሎች ርእሶችም ተካተዋል። ከሚቀጥለው ድምጽ ያድምጡ።