በእስር ላይ የሚገኘው የሀዲያ ሚዲያ ሃውስ ዩቲዩብ ባለቤት አቶ መለስ አብርሀም ከቀረቡበት ሦስት ክሶች በሁለቱ "ነጻ" ሲባል ፣ ርእሰ መስተዳደሩ በመተቸት በሚለው በአንዱ ክስ እንዲከላከል ብይን ተሰጠ።
የመከላከያ ምስክሮቹን እንዲያሰማም የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትላንት ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ባስቻለው ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ተከሳሹ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤት ቢወስንም፣ አኹንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ወንድሙ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጿል። ከክልሉና ከዞኑ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም