የኢትዮጵያ መንግስት እንደ አዉሮፓ አቀጣጠር በ2009 ዓም ስላወጣዉ የጸረ ሽብር ሕግ የተነተኑልን ፕሮፌሰር አድኖ አዲስ ሕግ የተለጠጠና የጋዜጠኞችን ብቻ ሳይሆን የሕብረተ ሰቡንም መብት የጣሰ ነዉ ይላሉ። አንድ ሰዉ ነጻ በአገሩ ጉዳይ እንዲሳተፍ ከተፈለገ ሃሳቡን በነጻነት ማሰራጨት መቻል አለበት፥ ነጻ ሰዉ ነዉ ሊባል የሚችለዉም የመናገር የመጻፍና ሃሳብ የመቀያየር መብቱ በመንግስት ወይም በሌላ ግለሰብ ሳይገደብ ብቻ ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሕዝብ የመሪዎቹ ቀጣሪ ነዉ፥ ጥሩ ሰራ አልሰራም ብሎ መገምገም የሚያስችለዉ ደግሞ ነጻ ሚዲያ ነዉ በማለት ያብራራሉ ፕሮፌሰር አድኖ አዲስ።
ፕሮፌሰር አድኖ አዲስ በሉዚያና የቱሌን ዩኒቨርሲቲ የRay Foresster የህግ ትምህርት ቤት ሊቀመንበርና ፕሮፌሰር ናቸዉ፥ ከቱሌን በተጨማሪም በሌሎች እዉቅ የአሜሪካ የትምህርት ተቋማት ለምሳሌ በዱክ፥ በኮርኔል እንዲሁም በቦስተን ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በHong Kong City University እና በአዉስትራሊያ ዩኒቬርሲቲዎች በMacqarire እና Melborne ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕግና ሕገ መንግስት አስተምረዋል። ፕሮፌሰር አድኖ አዲስ ከትዝታ በላቸዉ ጋር ያደረጉትን ዉይይት ያድምጡ።