በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደግል ለማዞር የነበረው ዕቅድ እንዲዘገይ መደረጉ ተገለጠ


ኢትዮ ቴሌኮም
ኢትዮ ቴሌኮም

ከዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በቅርብ ጊዜያት በአገር ውስጥም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተፈጠሩ እና በፍጥነት እየተቀያየሩ ባሉ ኢኮኖሚያው ለውጦች ሳቢያ መሆኑን የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ ዛሬ አርብ በትዊተር ባወጣው መግለጫ አስረድቷል።

አያይዞም መግለጫው የኢትዮጵይ መንግሥት በአቢዩ ኢኮኖሚ ዘርፍ የታየውን መሻሻል ታሳቢ በማድረግ እና የኢትዮ ቴሌኮምን ኢኮኖሚያዊ ክንዋኔ በቀጣይነት በማሻሻል ጊዜ መውሠድ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ወገኖች በሙሉ በተለይም ለኢትዮጵያ ህዝብ የተሻለ ዋጋ ለማስገኘት እንደሚበጅ አምኖ የወሰደው ውሳኔ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ወደግል ይዞታ የማዛወሩን ዕቅድ በዳር ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጾም ፍላጎት እንዳላቸው ካሳዩት አካላት ጋር ሂደቱን ይቀጥላል ሲል መግለጫው አክሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አርባ አራት ሚሊዮን ተገልጋይ ያለውን ኢትዮ ቴሌኮምን ለግል ዘርፍ መክፈት ተቋሙን በተሻለ ተወዳዳሪ እና የተቀላጠፈ ያደርገዋል በማለት ባለፈው ሰኔ ወር አርባ ከመቶውን ድርሻ ለመሸጥ በጀመረው ሂደት በርካታ ተጫራቾች ቀርበው እንደነበር ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

ስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል እና በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ ስምንት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ለመመደብ ቃል የገባው ግዙፉ የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባኒያ ሥራውን እንዲጀምር ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG