በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚ ዐብይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክል ፓምፔዮ ጋር ተወያዩ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክል ፓምፔዮ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክል ፓምፔዮ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክል ፓምፔዮ ትላንት ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤታ ያወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አንድ መቶኛው የሰለም ኖቤል ሽልማት ተረካቢ በመሆናቸው፣ እንኳን ደስ ያልዎት ብለዋቸዋል ይላል መግለጫው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ መካካል ያለው ጠንካራ ግንኙነት ጠቃሚነት ላይ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ለተካሄደው “ታሪካዊ ለውጥ” ላሉት ባላት ድጋ ፍላይ ጫና ሰጥተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክል ፓምፔዮ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክል ፓምፔዮ

በቅርቡ ኦሮምያ ላይ ስለተካሄደው ግጭትም እንደተነጋገሩ የቃል አቀባያቸው ጽህፈት ቤት ያወጣው መገለጫ ጠቁሟል። የዘር ግጭት ተግዳሮን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚያስፈልግ ተነጋግረዋል። ዶክተር ዐብይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስለ ቀጠናዊ ጉዳዮችም ሃስብ ተለዋውጠዋል።

የደቡብ ሱድን የሰላም ሥምምነት በሚጠይቀው መሰረት የብሄራዊ አንድነት መንግሥት በዘላቂነት ተግባራዊ እንዲሆን በማስተባበር በኩል ፓምፔዮ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እርዳታ መጠየቃቸውን መገለጫው ገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG