በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ባህር እንዲህ ከፍሎንም እንባችንና ሳቃችን አንድ መኾኑ አስገርሞኛል” ገጣሚና ደራሲ በረከት በላይነህ


አርቲስት ግሩም ዘነበ ከመድረክ ጀርባ በዝግጅት ላይ እያለ
አርቲስት ግሩም ዘነበ ከመድረክ ጀርባ በዝግጅት ላይ እያለ

በኢትዮጵያ በተለይ ወጣቶችን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንዲነቁ በማስቻሉና በውስጠ ወይራ መልእክቱ የሚታወቀው “ፌስታሌን” የተሰኘው አንድ ሰው ብቻውን የሚተውንበት የሙሉ ሰዓት የመድረክ ተውኔት ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ መጥቷል። በትናንትናው ዕለትም ዋሽንግተን ዲስ ውስጥ 900 ሰው ተመልክቶታል።

“እያዩ ፈንገስ” የተባለው ገፀ ባህሪ “ፌስታሌን” ሆኖ የሙሉ ሰዓት ተውኔት እስኪሆን ድረስ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በየወሩ በሚቀርበው ግጥምን በጃዝ ላይ ለሁለት ዓመት በ25 ክፍል ለተመልካች እይታ ቀርቧል።

የዚህ ገፀ ባህሪ ፈጣሪ ደራሲ፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ በረከት በላይነህ ነው። በአንቲገን፣ ንጉስ አርማህ፣ፍቅርን የተራበና በበርካታ የመድረክ ትያትሩ የትወና ብቃቱ የሚታወቀው አርቲስት ግሩም ዘነበ ደግሞ ብቻውን መድረክ የሚቆጣጠርበት ሥራው ነው።

በተውኔቱ ላይ የማይወቀስ የማይነቀስ የለም። ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ችግሮች ተጠያቂ የሚያደርገው ሁሉንም ነው። ጽዮን ግርማ በመክፈቻው ላይ ተገኘታ ተከታዩን ዘግባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

“ባህር እንዲህ ከፍሎንም እንባችንና ሳቃችን አንድ መኾኑ አስገርሞኛል” ገጣሚና ደራሲ በረከት በላይነህ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:10 0:00

XS
SM
MD
LG