በቅርቡ የቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገልፀዋል፡፡
ሁለቱ ታሳሪዎች “ከፍተኛ ሕመም እየተሰማቸው ነው ወደ ቂሊንጦ የተዛወሩት” ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በተለይ አቶ ዮሐንስ የሚገኙበት ማቆያ ሥፍራ ለጤንነታቸው የሚያሰጋቸው እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ እንዲቀየር ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልፀዋል፡፡ የቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ዳይሬክተር ኮማንደር ዓለምሰገድ፣ ውንጀላውን አስተባብለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም