የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በትጥቅ ትግል ላይ ለሚገኙ ኃይሎች በድጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ፣ አስተያየት የሰጡን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች “መንግሥት ቁርጠኝነት ይጎድለዋል” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በፓርቲያቸው አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ዝግጅት ላይ በአማራና በኦሮሚያ ክልል ላሉ የትጥቅ ታጋዮች ባስተላለፉት መልዕክት “አንድ ሺህ ዓመት ቢታገሉ ስለማያሸንፉን፣ ወደሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቀርብላቸዋለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡን ሦስት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች በበኩላቸው፣ በመንግሥት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ቢቀርቡም፣ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ግን አይስተዋልም ብለዋል፡፡
ተፋላሚ ወገኖች ለሰላም ድርድር የየራሳቸው ኃላፊነት ቢኖርባቸውም፣ መንግሥት የመሪነቱን ሚና መወጣት እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም