አዲስ አበባ —
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በተጨማሪም በድምር ውጤትም የ8.5 ከመቶ ዕድገት ሊኖር እንደሚችል ተናግረዋል።
ኤርትራን በተመለከተም በቅርቡ ተከስቶ የነበረው ግጭት የተጫረው በኤርትራ ምክንያት መሆኑን የጠቆሙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር “ተቀምጠን እንነጋገር” የሚለው ፖሊሲ አለመቀየሩን አመልክተዋል።
“ወረራውን ቀድማ ያካሄደችው ኢትዮጵያ ነች” ሲሉ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ባሠራጩት መልዕክት አመልክተው “ኢትዮጵያ በግልፅ ልትወገዝ ይገባል” ብለዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡