በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአልቃይዳ ሕዋስ በኢትዮጵያ መገኘቱን አስታወቁ


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ አልቃይዳ ሕዋስ እና ስለ ደቡብ ተፈናቃዮች ጉዳይ ተናገሩ፡፡

ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር የሃይማኖት አክራሪነት በእንጭጩ መቀጨት እንዳለበት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአልቃይዳ ህዋስ ተገኝቷል ብለዋል።

በቤንች ማጂ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ የሠፈሩ አርሶ አደሮችን በተመለከተ በክልሉ አመራር የተሰጠውን ማብራሪያ የደገፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዳንድ ድርጅቶች በጉዳዩ ላይ የያዙትን አቋም ተችተዋል።

በዛሬው ዕለት መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያዊያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ኢዴፓ) ግን አርሦ አደሮቹን በማፈናቀል የመብት ጥሰት የፈፀሙ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ጥሪ አቅርቧል።

ከአዲስ አበባ የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG