በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአርበኞች የድል በዓል መታሰቢያ ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን እንዲያጸኑ ጥሪ ቀረበ


በአርበኞች የድል በዓል መታሰቢያ ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን እንዲያጸኑ ጥሪ ቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:58 0:00

በአርበኞች የድል በዓል መታሰቢያ ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን እንዲያጸኑ ጥሪ ቀረበ

ኢትዮጵያዊው የዘመኑ ትውልድ አንድነቱን በመጠበቅ እና በማጠናከር ላይ ትኩረት እንዲያደርግ፣ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ዛሬ ዐርብ፣ ሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐዲስ አበባ የድል ሐውልት ታስቦ በዋለው የኢትዮጵያውያን የድል በዓል ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት ፕሬዚዳንቷ፣ ሳይከፋፈሉ ለአንድ ዓላማ መሥራት ለጋራ ድል እንደሚያበቃ፣ ትውልዱ ከቀደምት ወላጆቹ ሊማር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ በምትገኝበት በዚኽ ወቅት፣ “አርበኝነት ለጽናት እና ለድል” በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዘንድሮው የአርበኞች የድል በዓል ላይ ያገኘናቸው ተሳታፊዎችም፣ የዛሬው ትውልድ ችግሮቹን እንዴት መቅረፍ እንዳለበት፣ ከቀደምቶቹ ልምድ መቅሰም እንዳለበት፣ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አካፍለዋል፡፡

ከታሪካዊው የዓድዋ ድል አራት ዐሥርት ዓመታት በኋላ፣ በፋሺስት ጣሊያን ሁለተኛ ወረራ ተደፍሮ የነበረው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ በአርበኞች ያልተቋረጠ ተጋድሎ የተመለሰበት 82ኛው የአርበኞች መታሰቢያ የድል በዓል፣ ዛሬ ዐርብ፣ ሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሐውልት አደባባይ በብሔራዊ ደረጃ ተከብሯል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት እና አዳጊ ወጣቶች በሰጡን አስተያየት፣ የአሁኑ ትውልድ ከቀደምት እናት እና አባቶቹ፣ የሕዝብንና የሀገርን አንድነት መጠበቅን ሊማር ይገባል፤ ብለዋል፡፡

ዛሬ ላይ በየሰበቡ የሚስተዋለው መለያየት እንደሚያሳስባቸው የተናገሩ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች፣ ትውልዱ፥ የቀደምቶቹ የድል ምስጢር አንድነታቸው መኾኑን ሊያስተውል እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡

ቀደምት ኢትዮጵያውያን አርበኞች፣ የኢጣልያን ወራሪ ድል የነሱበት 82ኛ ዓመት በዓል እየተከበረ ያለው፣ አገሪቱ በተለያዩ በፈተናዎች ውስጥ ባለችበት ወቅት ነው፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በሰላም ስምምነት ከተቋጨ ስድስት ወራትን ቢያስቆጥርም፣ ግጭቶች፣ የሰላማዊ ዜጎች ሞት፣ ጉዳት እና መፈናቀል፣ ዛሬም በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይስተዋላል፡፡

በአርበኞች መታሰቢያ የድል ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴም፣ ትላንትን ከዛሬ ጋራ በማስተሳሰር መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በየዓመቱ፣ ሚያዝያ 27 ቀን በሚከበረው የኢትዮጵያውያን የድል በዓል 82ኛ ዓመት መታሰቢያ ላይ፣ በዓሉን የሚዘክሩ ልዩ ልዩ ትርዒቶችም ቀርበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG