በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖለቲካ መሪዎች እሥርና ይዞታ ፓርቲዎቹን እያሳሰበ ነው


የታሠሩ የፖለቲካ መሪዎች /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
የታሠሩ የፖለቲካ መሪዎች /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

ሰማያዊ ፓርቲ - አንድነት - አረና
ሰማያዊ ፓርቲ - አንድነት - አረና

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከፍተኛ የአመራር አባሉ አቶ አብረሃ ደስታ ባለፈው ሣምንት መቀሌ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ ከተወሰዱ በኋላ የተወሰዱበትን ማወቅ አለመቻሉን አረና ትግራይ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት አስታውቆ ነበር፡፡

አባሉ የተያዙበትን እሥር ቤት ሰሞኑን ማረጋገጡን የገለጠው አረና ጠበቃ የማማከር ሕገመንግሥታዊ መብታቸው ግን ተነፍጓል ሲል ፖሊስን ከስሷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ባለፈው ሣምንት በተመሣሣይ ሁኔታ የተሠሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች የአንድነቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ኃላፊው አቶ ዳንኤል ሺበሺና የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ እስከአሁን ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውን ድርጅቶቹ አስታውቀዋል፡፡

ተከሣሾች በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ ሕገመንግሥታዊ መብታቸው ያለመከበሩን መሠረት ያደረገው የተከሣሾች ጠበቃ በበኩሉ በመሠረተው አካልን ነፃ የማድረግ አቤቱታ ወይም ሃቢየስ ኮርፐስ የሕግ ሂደት የያዛቸው ክፍል ቀርቦ መልስ እንዲሰጥ ለነገ፣ ማክሰኞ ሐምሌ 8/2006 ዓ.ም አዝዟል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG