በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ለድርቅ ከጠየቀቸው እርዳታ 25 ከመቶውን ብቻ እንዳገኘች ታወቀ


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአገሪቱ አንዳንድ አከባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም መንግስታቸው በራሱ አቅምና ከውጭ በሚገኝ እርዳታ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። የሁለት ሺህ አራት አም ባጀት ትላንት በፓርላማው ሲጸድቅ የተናገሩት አቶ መለስ በምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎችም ማብራርያ ሰጥተዋል።

ለድርቁ ረድኤት የተጠየቀው በአመቱ መጀመርያ ላይ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ገልጸዋል። "ያስፈልገናል ብለን ከጠየቅነው እርዳታ 25 ከመቶውን ብቻ ባገኝንበት በአሁኑ ወቅት በራሳችን አቅም የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ጥረት እያደረግን ነው።" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG