በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ፓርላማ አምስት ድርጅቶችን በሽብርተኝነት ፈረጀ


የሦስቱ ተጠሪዎች መልስ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፓርላማ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ አምስት ቡድኖችን ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ አልሸባብና አልቃይዳን ሀገሪቱ ላይ በሽብርተኝነት ከባድ ስጋት የደቀኑ ሲል ሰይሟል ።

ድርጅቶቹ በተጠቀሰው መንገድ የተሰየሙት በሁለት ሽህ አንድ ዓመተ ምህረት በወጣው የፀረ ሽብርተኛ አዋጅ መነሻነት መሆኑን በፓርላማው የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ወይዘሮ አስቴር ማሞ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፓርላማ በሽብርተኝነት ከፈረጃቸው አምስት ድርጅቶች የሦስቱን ምላሽ አግኝተናል።

የግንቦት 7 ድርጅት ሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ ዶክተር በያን አሶባ እና የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለአሜሪካ ድምፅ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG