በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓርላማው የረቡዕ ውሎና የተጠቃሾች መልሶች


“ምድረ ነውጠኛ … አመፅ ተቀሰቀሰ ብሎ ቋምጦ ነበር …” - መለስ ዜናዊ፡፡ “አልቃይዳ ማለት እኛ የማናውቀው ድርጅት ነው” -- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጠሯቸው አካባቢዎች በአንዱ የማኅበረሰብ መሪ፡፡ “የፈጠራ ወሬ ማውራቱን ከቀጠለ የሌላ አገልጋይ መንግሥት ጋር ምንም ጉዳይ የለንም” - የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር፡፡

በቅርቡ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተደረገው የሥራ ማቆም አድማ ፖለቲካዊ ግፊት ጭምር ነበረበት ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተናገሩ፡፡

ከሥራ የተባረሩት መምህራንም የብቃት ችግር የነበረባቸው ናቸው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሌሎች ጉዳዮች ላይም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ በማክሰኞ የፓርላማ ንግግራቸው በኢትዮጵያ የሃይማኖት አክራሪነት እየተከሰተ መሆኑን ጠቅሰዋል። በጥቂት የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮችና በሰላፊ ሙስሊሞች አክራሪነት እየተስፋፋ ነው ብለዋል።

አልቃይዳ በብዛት የሰላፊ ተከታይ እንደሆነና መንግሥታቸው በባሌና በአርሲ የአልቃይዳ ህዋስ እንዳገኘ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጠቀሷቸው የኦሮሚያ ዞኖች በአንዱ የሚኖሩ “ለደህንነቴ እሠጋለሁ” በማለት ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የሙስሊም ማህበረሰብ መሪ በበኩላቸው የአልቃይዳ ህዋስ በባሌም ሆነ በአርሲ መገኘቱን አስተባብለዋል።

“የመንግሥት ዓላማ ኢትዮጵያን በውስጥ የማሸበር ዕቅድ አካል ወደ አገር ገብቶ ሳይሆን አብዛኛው የኦሮሞ ህዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ስለሆነ እንዳለ በዚህ ስትራተጂ አጠፋዋለሁ የሚል ነው” ብለዋል። “እስላም ማለት ሰላም ነው” ሲሉ ቃላቸውን የሰጡን “ሰላም ማለት ደግሞ ከመንግሥትና ከሕዝብም ጋር ለዓለም ሁሉ ነዉ” ሲሉ አብራርተዋል።

“አልቃይዳ እና ሌሎች አሸባሪዎች በዓለም ላይ ያደረሱትን ጥቃት እኛ የምንደግፍበት ምንም ምክንያት የለንም፤ አልቃይዳ የማናውቀው ድርጅት ነው፤ ከአርሲና ከባሌ የእስልምና ተከታዮች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም” ብለዋል።

ይልቁንም የመንግሥት ካድሬዎች በየወረዳውና ቀበሌው የአህባሽ እስልምና ተከታዮች መሆን አለባችሁ በማለት ህዝብን በማስገድድ ስለሚያንገላቱ፣ መንግሥት ይህን በማስፈፀም በግል ኃይማኖት ጣልቃ መግባቱን እንቃወማለን” ብለዋል።

ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ

XS
SM
MD
LG