ዋሽንግተን ዲሲ —
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትና የክልል ጠቅላይ ኦዲተር መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት በጀት አጠቃቀምን በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያቀርቡት ዓመታዊ ሪፖርት፤ በቢሊዮን የሚቆጠር የገንዘብ ጉድለት፣ ያልተወራረደ የሒሳብ ሰነድ መኖርና ገንዘቡ ለታቀደለት ሥራ ያለመዋሉን የሚያሳዩ ተደጋጋሚ ሪፖርቶችን ያቀርባል።
በቅርቡም የወጡት ሪፖርቶች የሚያሳዩት ይህንኑ ነው። ጉድለቱን ይፋ በሚያደርግበት ጊዜም ዐቃቤ ሕግ ወይም ፀረ ሙስና ኮሚሽን በጉዳዩ ገብቶ እንዲያጣራም ምክረ ሐሳብ ይለግሳል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው ሁለት ምሑራን ግን የመሥሪያ ቤቱ የጉድለት ሪፖርት ከዓመት ዓመት እየጨመረ ከመምጣት ውጪ በጉድለቱ የተጠየቀ አካል አላየንም ይላሉ። “በዚህ በኩል ግብር እየሰበሰቡ በሌላ በኩል ጎደለ ማለት በሀገሪቱ ተጠያቂነት ያለበት አሠራር አለመኖሩን ማሳያ ነው” ብለዋል።
ምሑራኑን ያነጋገረቸው ጽዮን ግርማ ተጨማሪ ዘገባ አላት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ