ዋሺንግተን ዲሲ እና አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ ፓርላማ የ2013 ዓ.ም.ን በጀት ዛሬ አፅድቋል። በሃገሪቱ የወቅቱ ሁኔታ ላይ ያደረጉትን ንግግርም አዳምጧል።
በዛሬው የፓርላማው ውሎ ላይ ድንገት ተገኙ የተባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወቅቱ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከሃገር ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “የኦሮሞን ህዝብ የመከፋፈልና ኢትዮጵያዊያንን የመከፋፈል” ያሉትን ቅስቀሳ አቁመው ሃገር ውስጥ ገብተው በሰላም እንዲታገሉ ጠይቀዋል።
የኦሮሞ ህዝብ ለመቶ ዓመታት ታግሎ አሸንፏል፤ የትጥቅ ትግልና ጦርነት ከእንግዲህ አያስፈልገንም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በዛሬው ጉባዔ ላይ የአዲሱ ሲዳማ ክልልና የነባሩም የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልል ጉዳዮችና በጀት፣ የኮቪድ-19ና የምርጫው ጉዳይም ተነስተው ነበር።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።