በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ምክር ቤት በአገሪቱ የ 2004 አም ረቂቅ ባጀት ላይ ተወያየ


የኢትዮጵያ ፓርላማ በ 2004 አም የአገሪቱ ረቂቅ ባጀት ላይ በልዩ ስብሰባ ተወያይቷል። በውይይቱ ወቅት ሀሳብ እንዲሰጡበት በቅድሚያ የተጠየቁት ብቸኛውን የተቃዋሚ መቀመጫ የያዙት አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው።

"ለክልሎች የመቶ አመቱን ግብአት ለማሳካት በገንዘብና በኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በኩል የሚደረገውን የካፒታል ፕሮጄክት ድጋፍ በዋነኝነት የክልሎቹን በህገ መንግስት የተሰጣቸውን ባጀት ላይ የመወሰን ነጻነት የሚገድብ ነው። ስለሆነም ይህ ባጀት ከፖሊሲ አንጻር ተቀባይነት የለውም የሚል እምነት አለን" ሲሉ ገልጸውታ።

የፌደራሉ መንግስት የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሶፍያን አሕመድ በበኩላቸው "ለክልሎች የሚሰጠው ይህ የ 15 ቢልዮን ብር የባጀት ድጎማ ከፖሊሲ አኳያ የክልሎችን የመወሰን ስልጣን የሚጋፍ አይደለም ሲሉ አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG