በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ የአየር መንገድ ቀዳሚ መዳረሻ - ኢትዮጵያ

A worker carries a decorative crown prior to placing it atop a flag pole ahead of planned celebrations for Queen Elizabeth's Platinum Jubilee, facing Buckingham Palace, in London, Britain.
A worker carries a decorative crown prior to placing it atop a flag pole ahead of planned celebrations for Queen Elizabeth's Platinum Jubilee, facing Buckingham Palace, in London, Britain.

ኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የሚጓዙ የአየር ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን በማስተናገድ ቀዳሚነቱን ከዱባይ ተረከበች። ለዚህም - በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እየተወሰደ ያለው የለውጥ እርምጃ በዓለምቀፉ ማኅበረሠብ የተሰጠው በጎ ምላሽ አስተዋፅዖ እንዳበረከተ ተመልክቷል።

ኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የሚጓዙ የአየር ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን በማስተናገድ ቀዳሚነቱን ከዱባይ ተረከበች። ለዚህም - በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እየተወሰደ ያለው የለውጥ እርምጃ በዓለምቀፉ ማኅበረሠብ የተሰጠው በጎ ምላሽ አስተዋፅዖ እንዳበረከተ ተመልክቷል።

ፎርዋርድኬይ ይህን ውጤት ይፋ ያደረገው በቀን ውስጥ የተጓጓዙ የአየር ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን መረጃ ከገመገመ በኋላ መሆኑ ተዘግቧል። በዚህም በአዲስ አበባ በኩል ከሠሃራ በታች ወደሚገኙ ሀገራት የሚጓዙ ሰዎች ቁጥር ከፈረንጆቹ 2013 ወደ 2017 - የ85 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።

በተመሳሳይ እነዚህን ተጓዦች በማስተናገድ ቀዳሚ የነበረችው ዱባይ በተመሳሳይ ጊዜ የ 31 በመቶ እድገት ማሳየቷን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል።

በተለይም ኢትዮጵያ - አፍሪካውያን በመዳረሻ አውሮፕላን ማረፊያ ቪዛ እንዲያገኙ መፍቀዷ እና በኦንላይን የቪዛ አገልግሎት መጀመሯ - እንዲሁም በመንግስት ቁጥጥር ስር የነበሩ ግዙፍ ተቋማት ለግል ባለሀብቶችን ክፍት እንደምታደርግ መግለጿ - ለአድገቱ ምክንያት ሆነዋል ነው ትብሏል።

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እየሰፋ መምጣት ከዚህ ቀደም ከሰሜን አሜሪካ ወደ አህጉሪቱ የሚመጡ አፍሪካውያን በለንደን፣ ፓሪስ እና ፍራንክፈርት የሚያደርጉትን እረፍት በመተው ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ መብረር መጀመራቸውም ተመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG