በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት - ገናን በማክበር ላይ ሲኾኑ፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተከታታይ ግጭቶች በሚታዩበት የአፍሪካ ቀንድ ክፍል ሠላም እንዲመጣ ጸልየዋል።
በሺሕዎች የተቆጠሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በሙሉ ነጭ ልብስ በአሸበረቀ አለባበስ ደምቀው በእጆቻቸው የጧፍ መብራት ለኩሰው፣ በጸሎትና በዝማሬ አክብረዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ በዋዜማው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የጎሳና ሌሎችም ግጭቶች በሚስተዋልባት ሃገር ሰላምና እርቅ ይወርድ ዘንድ ጥሪ አድርገዋል።
በቅርብ ጊዚያት ውስጥ በሀገሪቱ የታየው የመሬት ናዳ ፣ መንቀጥቀጥ እንዲሁም ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅለዋል።
በትግራይ ክልል ያለው ጦርነት በሠላም ስምምነት ቢቆምም፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም በሌሎች ሥፍራዎች የሚስተዋሉ ግጭቶች በርካቶችን ለአስከፊና የተስፋፋ ስቃይ ሲያጋልጥ፣ የሕፃናት አድን ድርጅቱ (ዩኒሴፍ) እንደሚለው 9 ሚሊዮን ሕፃናት ከትምህርት ውጪ እንዲሆኑ አድርጓል።
በቤተ ክርስቲያኒቱ የተገኙ ምዕመናኑም ሰላም ለሀገራችው እንዲመጣ ጸልየዋል። ልዑል ተስፋ በዘንድሮው አከባበር ላይ በመገኘኑቱ ደስታ ተሰምቶታል።
ቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተገኙት ዓማኞች፣ ጣፍና ሻማ በእጃቸው በዝማሬና በጸሎአት ምስጋና እና ልመናቸውን ለእግዚያብሔር አቅርበዋል።
ምናለም እሸቱ በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታይ ስትኾን "የአእላፋት ዝማሬ" በሚል በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ዘማሪያን በተሰናዳዝ ዝግጅት ላይ ተገኝታ በዓሉን አክብራለች። ዝግጁቱ ቀጣይነት እንደሚኖረው ተስፋን በመሰነቅ ለነገ በጎ ተመኝታለች።
በሺሕ የሚቆጠሩ ምዕመናን በታደሙበትና አዲስ አበባ በሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን የተገኘችው አልማዝ ዘውዴ ለሠላም እንደምትጸልይ ተናግራለች፡፡ የ43 ቀናት ጽም መፈታቱንና የእየሱስ ክርስቶስ ውልደትን ለማክበርም ነጭ ባህላዊ ልብሷን ለብሳለች፡፡
በጎንደር ከተማ ነጋዴ የነበረችው አልማዝ፣ በአማራ ክልል በመንግስት ኅይሎችና በአካባቢው በሚገኙ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደው ግጭት ያስከትለውን ሰቆቃ በተመለከተ ስትናግርም፣ “ጓደኞቼንና ኑሬዬን አጥቻለሁ” ብላለች፡፡
በአዲስ አበባ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቄስ የሆኑት ኢሳያስ ስዩም ደግሞ፣ ገና ለራስ ምግብ ከመመገብና ከራስ ደስታ በላይ እንደሆነ፣ ከተቸገሩት ግራ መአድ መጋራትና፣ በአዲስ አበባ በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙትን ጨምሮ በግጭት ምክንያት ችግር ላይ ከወደቁ ወገኖችን መርዳት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩት በዓላት፣ ገና በደማቅነቱ ይወሳል፡፡ ስያሜው፣ "ጌና" ከሚለው የግሪክ ቃል የተወረሰ ሲኾን፣ ትርጉሙም ልደት ማለት ነው። ቃሉ የአረብኛም መሠረት እንዳለውና ምስጋና፣ ብልጥግና የሚል ትርጉምም እንዳለው ሊቃውንቱ ያስረዳሉ። ገና፣ ከመንፈሳዊ ይዘቱ ባሻገር ያለው ማኅበራዊ እና ባህላዊ ክንዋኔው በብዙኀኑ ዘንድ ተናፋቂ ያደርገዋል።
መድረክ / ፎረም