በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ግጭቶች ሕይወት ጠፋ


Gunung berapi Cotopaxi di Ekuador saat memuntahkan abu vulkanik, diambil dari kota Tambillo, Ekuador.
Gunung berapi Cotopaxi di Ekuador saat memuntahkan abu vulkanik, diambil dari kota Tambillo, Ekuador.

በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በዋና ከተማይቱ ማስተር ፕላን ውስጥ አካትቶ ለማልማት በሚል የተያዘውን ዕቅድ ከተቃወሙ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተነሣ ግጭት በሰው ይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የመንግሥት ኮመዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡


የኦሮሚያ ተማሪዎች ተቃውሞ - መቱ
የኦሮሚያ ተማሪዎች ተቃውሞ - መቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በዋና ከተማይቱ ማስተር ፕላን ውስጥ አካትቶ ለማልማት በሚል የተያዘውን ዕቅድ ከተቃወሙ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተነሣ ግጭት በሰው ይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

ፅ/ቤቱ ሐሙስ፣ ሚያዝያ 23/2006 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በመዳ ወላቡ የሦስት ተማሪዎች፣ በአምቦና ቶኬኩታዮ ከተሞች የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በቢዝነስና ኮንስትራሽን ባንክ ላይ የዘረፋ ሙከራ መደረጉን ገልጿል፡፡

በሃረማያ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በተወረወረ ፈንጂ የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉንና ሌሎች ሰባ ተማሪዎች መቁሰላቸውን ፅ/ቤቱ በዚሁ መግለጫው አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በአምቦና አካባቢዋ “ቁጥራቸው 17 የሚደርስ ሰዎች ተገድለዋል” ሲል የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ - ኦፌኮ ከስሷል፡፡
ኦፌኮ የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ “የኢሕአዴግ መንግሥት ለዚህ የኃይል እርምጃ ተጠያቂ ነው” ብሏል፡፡

መግለጫው አክሎም “የኦሮሞና የአማራ ብሔረሰቦችን ለማጋጨትም ደባ እየተካሄደ ነው” ብሏል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG