በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተፈናቃዮቹ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የጅጂጋ ጉዞ ላይ ብዙ ጥያቄ አላቸው


ጅግጅጋ ከተማ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የጅጂጋ ክልል ፕሬዝዳንት ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር
ጅግጅጋ ከተማ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የጅጂጋ ክልል ፕሬዝዳንት ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር

ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በሐማሬሳ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በተፈናቀሉበት ወቅት የተገደሉ ሰዎች ገዳዮች ለፍርድ ሳይቀርቡ፣ ጥለውት የወጡት ንብረት እስካሁን የታሰሩ ሰዎችን በተመለከተ እጅግ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል። አያይዘውም ከተፈናቀሉ ጀምሮ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀው ቀጣይ ሁኔታቸውን አለማወቃቸውም እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።

እሁድ ዕለት የመጀመሪያ የሥራ ጉብኝታቸውን ወደ ጅግጅጋ ከተማ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የጉብኝቱ ዓላማ በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች አዋሣኝ ወረዳዎች ላይ ለተከሰቱ ግጭቶችና ለተከተለውም ቀውስ ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት እንደሆነ ተገልጿል።

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉና በአሁኑ ወቅት በሐማሬሳ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በሁኔታው ግራ እንደተጋቡ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

ተፈናቃዮቹ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉዞ ላይ ብዙ ጥያቄ አላቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG