በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው


ምዕራብ ወለጋ ዞን
ምዕራብ ወለጋ ዞን

በአንዳንድ የምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ሰላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡

ምዕራብ ወለጋ ዞን
ምዕራብ ወለጋ ዞን

please wait

No media source currently available

0:00 0:01:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በአንዳንድ የምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ሰላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡

ሠልፎቹ በምዕራብ ሸዋ፤ በአምቦ፣ በጊንጪ፤ በምዕራብ ወለጋ ደግሞ በጃርሶ ወረዳና በመንዲም መካሄዳቸው ታውቋል፡፡

ሠልፉ የተደራጀው በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንደሆነና የሚመራው በተማሪዎች መሆኑን የገለጡ አንድ የጃርሶ ወረዳ ነዋሪ በዛሬው ሠልፍ ነጋዴዎች፣ ገበሬዎችና የመንግሥት ሠራተኞች መካፈላቸውን ተናግረዋል፡፡

ሠልፈኞቹ እያነሷቸው ያሉት ጥያቄዎች የማስተር ፕላን ጉዳይን፣ የግብር መጨመርን የያዙ ሲሆኑ ኦሮምኛ የፌደራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲሆንና ራስን የማስተዳደር ጥያቄዎችን ያካተቱ መሆናቸውን ነዋሪው ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

የዛሬው የጃርሶው ሠልፍ በሰላማዊ ሁኔታ መካሄዱን፣ የኦሮሚያ ፖሊስም በእርጋታ ይከታተል እንደነበረና ማምሻው ላይ ግን አሥር የሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት ደርሰው ሰልፉን በእንባ አስመጭ ጋዝ መበተናቸውን ከሥፍራው የደረሱን ጥቆማዎች አመልክተዋል፡፡

ትናንት መንዲ ላይ በተካሄደው ሠልፍ ሦስት ሰዎች በፀጥታ አስከባሪዎች ድብደባ ተጎድተው ነጆ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆናቸውን ሰማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት የጃርሶ ወረዳ ነዋሪው ገልፀዋል፡፡

የክልሉን ፖሊስ ኮማንደር ለማነጋገር የተረገው ጥረት አልተሣካም፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG