በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንዳንድ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ መሪዎች በፕሬዚደንት ኦባማ ንግግር ላይ የሰጡት አስተያየት

Merera and Yilkale
Merera and Yilkale

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በአፍሪቃ ሕብረት ባደረጉት ንግግርና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት ጋዜጣዊ ላይ በተነሱት ነጥቦች ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በአፍሪቃ ሕብረት ባደረጉት ንግግርና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት ጋዜጣዊ ላይ በተነሱት ነጥቦች ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

ፕሬዚደንት ኦባማ አወዛጋቢዉ የኢትዮጵያ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ በተጠናቀቀ አጭር ወራት ዉስጥ ወደ አገሪቱ መምጣታቸዉ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ለመሪዎቹ የሚተወዉ መልእክት አሳሳቢ እንደነበር የገለጹ አሉ።

በሌላ በኩል የአፍሪቃ አምባገነን መሪዎች ከፕሬዚደንት ኦባማ ንግግር ትምህርት ሊቀስሙ እንደሚችሉ በመጠቆም ፣ ሆኖም በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ተፈላጊዉን ለዉጥ እንዲያመጣ ጫና በመፍጠር ንግግሩ ሊኖረዉ የሚችለዉን ፋይዳ የጠየቁም ነበሩ።

በተጨማሪም ፕሬዚደንት ኦባማ ለትጥቅ ትግል ያላቸዉን ተቃዉሞ ለመጠቆም የኢትዮጵያን ምርጫ ዴሞክራዊያዊ ሲሉ መግለጻቸዉ ያስቆጣቸዉም መሪ ሃሳባቸዉን ሰጥተዋል።

ከመለስካቸዉ አመሃ ዘገባ ዝርዝሩን ያድምጡ

አንዳንድ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ መሪዎች በፕሬዚደንት ኦባማ ንግግር ላይ የሰጡት አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG