በኢትዮጵያ ኦለምፒክ ኮሚቴ እና በአምስት የኮሚቴው አመራሮች ላይ፣ ከፓሪስ ኦለምፒክ ጋራ በተገናኘ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ መስርተናል ሲሉ ጠበቆች ተናግረዋል።
ከከሳሽ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ጳውሎስ ተሰማ፣ በተከሳሾቹ ላይ ሌሎች ተጨማሪ ክሶችም እንደተመሰረቱ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡
የክሱ ሂደት፣ በመደበኛ ፍርድ ቤቶች መታየት እስኪጀምር ድረስ፣ በኢትዮጵያ ኦለምፒክ ኮሚቴ የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች እንዳይንቀሳቀሱ፣ እንዲሁም በግምቦት እና ሰኔ ወራት ጠቅላላ ጉባኤዎች የተላለፉ ውሳኔዎች እንዲታገዱ ተወስኗል ሲሉም አስረድተዋል።
የፕሬዝዳንቱን ጨምሮ የተከሳሹን የኦሎምፒክ ኮሚቴውን አጭር ምላሽም አካተናል። ከድምጽ ማጫወቻው ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም