በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ወሎ ዞን የዛሬ ውሎ- በመርሳ ወጣቶች መደብደባቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል


በሰሜን ወሎ በወልዲያ፣ በመርሳ፣ በቆቦና በሌሎች የዞኑ ከተሞች ውጥረት እስከዛሬ መቀጠሉንና ወጣቶች ከየቤቱ እየተለቀሙ እየታሰሩ መሆኑን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለጹ።

የሰሜን ወሎ ዞን የዛሬ ውሎ- በመርሳ ዛሬ ወጣቶች መደብደባቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:13 0:00

“በመርሳ የታሰሩ ይፈቱ” በሚል የጠየቁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ በታጣቂዎች መደብደባቸውን የዐይን እማኝ ነኝ ያሉ ነዋሪ ተናግረዋል። በከተሞቹ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ሆነ ንግድ ቤቶች መዘጋቱን በምትኩ በየፌዴራል አድማ በታኝና ነዋሪዎች “አጋዚ” እያሉ በሚጠሯቸው “ልዩ ሃይሎች” ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ይናገራሉ።

የመርሳ ከተማ ከንቲባ ከተማዋን ለማረጋጋት የሀገር ሽማግሌዎች ባሉበት ተነጋግረን ተስማምተን ተለያይተናል ብለዋል። ሽማግሌዎቹ የተስማማነው ነገር የለም ይላሉ።

ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG