በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ዓባይ ግድብን ለአራተኛ ግዜ ልትሞላ ነው


ዓባይ ግድብ
ዓባይ ግድብ

ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ላይ አራተኛ ዙር ሙሌት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ አስታውቀዋል።

4.2 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል የተባለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ አንስቶ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ተቃውሞ ቢገጥመውም፣ አገሪቱ ግንባታውን ቀጥላለች፡፡

“የህዳሴው ግድብ አራተኛ ሙሌት ተቃርቧል። ያለፉት ሶስት ሙሌቶች የታችኛው ተፋሰስ አገሮችን አላወኩም። ቀጣይ ሙሌቶችም የተለዩ አይሆኑም” ሲሉ ደመቀ መኮንን መናገራቸውን የኤኤፍፒ ሪፖርት አመልክቷል።

“የጋራ የሆነውን የአፍሪካ ወንዝ ለብቻ ለመጠቀም የሚሹ ኃይሎችን አሉታዊ ትርክት ተቋቁሞ፣ ፕሮጀክቱ ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ ነው” ሲሉ አክለዋል።

ኢትዮጵያ ሙሌቱን እንድታቆም ግብጽ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች፡፡

ደመቀ መኮንን በተናገሩበት ከፍተኛ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ከኡጋንዳ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ ሱዳን እና ታንዛኒያ ተገኝተዋል።

ሱዳንም ሆነች ግብጽ በጉባኤው ላይ እንዳልተሳተፉ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የሱዳኑ ፕሬዝደንት አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን፣ አዲስ አበባ እና ካርቱም በግድቡ ጉዳይ “በአንድ ላይ የተሰለፉ እና የተስማሙ ናቸው” ሲሉ ባለፈው ጥር መናገራቸውን ዘገባው አስታውሷል።

XS
SM
MD
LG