በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በድጋሚ ታገዱ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) የተባሉ፣ በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ላይ የሚሠሩ ሁለት ድርጅቶች የመጀመሪያ እግዳቸው በተነሳ በጥቂት ቀናት ውስጥ በድጋሚ መታገዳቸውን አረጋግጠዋል።

"ድርጅቶቹ የመጀመሪያው እግዳቸው ከተነሳላቸው ከቀናት በኋላ በድጋሚ የታገዱት ከዚህ በፊት የፈጸሟቸውን ጥፋቶች በመቀጠላቸው ነው” ሲል የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በጻፈላቸው ደብዳቤ አመልክቷል።

ሁለት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በድጋሚ ታገዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:19 0:00

የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ አምሃ መኮንን በበኩላቸው፣ “ገና ሥራ እንኳን ሳንጀምር በዝግጅት ላይ እያለን በድጋሚ መታገዳችንን የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሰን” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከል ዋና ዲሬክተር ያሬድ ኃይለማርያም፣ “ድርጅቶቹ ማሻሻያ አላደረጋችሁም ለማለት የሚያስችል ጊዜ አልተሰጣቸውም” ብለዋል። ባለ ሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥበት አሳውቆናል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG