በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታዬ አጽቀ ሥላሴ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ስድስተኛው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ስድስተኛው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ስድስተኛው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም. እየተካሄደ ባለው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ አዲሱን ኃላፊነታቸውን የተቀበሉት አምባሳደር ታዬ፣ ከተሰናባቿ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር የሥልጣን ርክክብ አድርገዋል።

አዲሱ ፕሬዚዳንት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን አገልግለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር በመሆን ማገልገላቸውንም በምክር ቤቶቹ የመክፈቻ ሥነ ሰርዓት ላይ የተነበበው ታሪካቸው ያሳያል። መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል።

ተሰናባቿ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለምን ለሁለተኛ የኃላፊነት ዘመን እንዳልቀጠሉ እስካሁን በይፋ የተገለፀ ነገር የለም።

የአዲሱ ፕሬዝዳንት ምርጫ ይፋ የተደረገውም፣ የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ያሰፈሩትን ጽሁፍ፣ በርካቶች በተለያየ መንገድ እየተነተኑ ባሉበት ወቅት ነው።

የአንጋፋውን ድምጻዊ መሀሙድ አህመድን "ዝምታ ነው መልሴ" የተሰኘ ዘፈን ስንኛች ያጋሩት የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት "ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" በማለት አጠቃለዋል።

የዚህን ዘገባ ሰፋ ያለ ክፍል በምሽቱ ዝግጅታችን ይዘን እንቀርባለን።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG