በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሾሙ


Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi (file photo)
Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi (file photo)

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉትን አቶ ሥዩም መስፍንን ተክተዋል።

በቅርቡ በተካሄደው የኢሕአዴግ ስምንተኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከአቶ መለስ ዜናዊ ቀጥሎ ያለው የፓርቲ ሃላፊነት ተሰጥቶአቸዋል። ከዚህ ቀደም በነበረው ልምድ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር የሃገሪቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆን ነበር።

አቶ ሃይለማሪያም ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እኩል ስልጣን ላይ የቆዩትን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍንንም ተክተዋል። ከሃያ ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሾሙት አቶ መለስ ዜናዊ ስለ አዲሱ ተሿሚ የስራ ልምድ ለፓርላማው አብራርተዋል።

በአዲሱ ካቢኔ ካልተካተቱ ሌሎች የቀድሞ ባለስልጣናት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰ፣ የንግድና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ ግርማ ብሩና የአቅም ግንባታው አቶ ተፈራ ዋልዋ ይገኙበታል።

ሥራቸው ላይ ከሚቆዩት መካከል የመንግስት ኮሚኒኬሽንስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ስምኦን፣ የአገር መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፤ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም ይገኙበታል።

ለዝርዝሩ የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG