በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪውን አሳልፋ ሰጠች


በህገወጥ መንገድ ኤርትራውያንን ከአፍሪካ ወደ ኔዘርላንድ በማዘዋወር መሪ ተዋናይ ነበር በመባል የተጠረጠረን አንድ የ38 ዓመት ኤርትራዊ ለደች የህግ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ አስረክባለች።

የዐቃቤ ህግ ቡድኑ ግለሰቡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኤርትራውያን ከአፍሪካ ወደ ኔዘርላንድ በህገወጥ መንገድ በማስገባቱ ጠርጥረነዋል ብሏል።

“የፍለሰተኞቹ ጉዞ በጨካኝ ሁከት የተሞላና፣ ህይወትን አደጋ ላይ በሚጥል የባህር ላይ ጉዞ የተሞላ ነበር” ሲሉም አክለዋል ዐቃቤ ህጎቹ።

የደች ዐቃቤ ህግ አክሎም፣ ምርመራው በጣሊያን፣ በኢንተርፖል፣ እና በዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ትብብር የተካሄደ ነው ብሏል።

ከእአአ 2014 እስከ 2020 በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠረውና ማንነቱ ያልተገለጸው ግለሰብ ዛሬ ኔዘርላንድ መድረሱና በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG