በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዑለማዎች ምክር ቤት የሼኽ ኢዘዲን የመውሊድ መልዕክት


መስጂድ
መስጂድ

ዛሬ የነብዩ መሐመድ 1444ኛ የልደት ቀን መውሊድ ነው፡፡ ዕለቱ በዓለም ዙሪያ ባሉ ሙስሊም አማንያን ዘንድ እየተከበረ ነው፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዛሬ የነብዩ መሐመድ 1444ኛ የልደት ቀን መውሊድ ነው፡፡ ዕለቱ በዓለም ዙሪያ ባሉ ሙስሊም አማንያን ዘንድ እየተከበረ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዑለማዎች ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሼኽ ኢዘዲን ሼኽ አብደልአዚዝ ሐይማኖታዊ መልዕክታቸውን በቪኦኤ በኩል አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዑለማዎች ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሼኽ ኢዘዲን ሼኽ አብደልአዚዝ በነብዩ መሐመድ ልደት፣ አስተዳደግና ባሕርያት ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ነብዩ ሰውን ከሰው አበላልጠውና ለይተው የማያዩ መሆናቸውን፤ ትልቅና ትንሽ፣ ሃብታምና ድኃ፣ ወንድና ሴት፣ እሥላምና ክርስቲያን ብለው የሚያበላልጡና አድልዎ የሚያደርጉ እንዳልነበሩ ገልፀዋል፡፡

ሼኽ ኢዘዲን በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መካከል ስለሚታየው ሁኔታና በእሥር ቤትም ስላሉ፤ እንዲሁም ሳዑዲ አረቢያ ስለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ስለተመለሱትም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፤ መልዕክቶችን አሰምተዋል፡፡

በኢትዮጵያዊያኑ ላይ ተፈፅሟል የተባለው አድራጎት ያሣዘናቸው መሆኑንና የእምነቱ መሪዎችም ከሳዑዲ አቻዎቻቸው ጋር የመመካከር ሃሣብ እንዳላቸው፤ የተመለሱትም ጥንካሬ እንዲኖራቸው መክረዋል፡፡

የሃይማኖቱ መሪዎችም ዱአ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብም ሰክኖ ጉዳዮቹን እንዲፈታ ሲሉ አሳስበዋል ሼኽ ኢዘዲን ሼኽ አብደልአዚዝ፡፡

ሼኽ ኢዘዲን ሼኽ አብደል አዚዝ ያስተላለፉትን መልዕክትና ቪኦኤ ከእርሣቸው ጋር ያደረገውን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG