ዋሺንግተን ዲሲ —
የታጠቁ የኢትዮጵያ ፖሊስና ደህንነት ሠራተኞች ዛሬ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው አንዋር መስጊድ የዓርብ ፀሎታቸውን ለማድረስ በወጡ ምዕመናን ላይ ድብደባና አፈሳ ማካሄዳቸውን እማኞች ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ምዕመናኑ «ድምፃችን ይሰማ» ባወጣው መርሃ ግብር መሠረት መሪዎቻቸው እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀረቡት እንደወትሮው በሰላማዊ መንገድ መሆኑን እነዚሁ እማኞች ያስረዳሉ።
ከአዲስ አበባ ፖሊስ ምላሽ ለማግኘት የዝግጅት ክፍላችን ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የሰሎሞን ክፍሌ ዘገባ ያዳምጡ፡፡