በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአወሊያ ዙሪያ ያለው ውዝግብ


ከአወሊያ የትምህርት ተቋም ጋር በተያያዘ ከሙስሊም አካላት ጋር የተለያዩ ውይይቶችን ሲያካሂድ የቆየው የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን “ደረስኩበት” ያለውን ይፋ አድርጓል፡፡

“አወሊያ ትምህርት ቤትን ያስተዳድሩ የነበሩ አንዳንድ የውጭ ተቋማት ድጋፍ በማድረግና በማስተማር አክራሪነትን ሲያስፋፉ ቆይተዋል” ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ሺፈራው ተክለማሪያም አስታውቀዋል።

“የተቋሙን አስተዳደር ከኢትዮጵያዊያን ላይ የወሰዱት እነዚህ የውጭ ኃይሎች የራሣቸውን የእምነት ፍልስፍና ሲያስፋፉበት ቆይተዋል” ብለዋል - ሚኒስትሩ፡፡

የዶ/ር ሺፈራው አስተያየት ያነጣጠረው እስካለፈው አንድ ዓመት ድረስ አወሊያን ሲያስተዳድር በነበረው ዓለምአቀፍ እሥላማዊ ተራድዖ ድርጅት ላይ ነው፡፡

በአወሊያ አካባቢ የተፈጠረውን ቅሬታ አስመልክቶ የተቋቋመው የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አቡበከር አህመድ መሃመድ ግን ለሚባሉት ነገሮች መረጃ ሊቀርብ ይገባል ብለዋል።

ለተጨማሪ ዝርዝር የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG