በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በመግባቢያ ስምምነቱ ተያያዥ ውጥረቶች ኢጋድ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቀች


ኢትዮጵያ በመግባቢያ ስምምነቱ ተያያዥ ውጥረቶች ኢጋድ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:29 0:00

ኢትዮጵያ በመግባቢያ ስምምነቱ ተያያዥ ውጥረቶች ኢጋድ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቀች

ኢጋድ ጠርቶት በነበረው ስብሰባ ያልተገኘችው ኢትዮጵያ፣ ሌላ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቀች። ኢትዮጵያና ሶማሊያ ከሶማሊላንድ ጋራ በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነትና ተያያዥ ውጥረቶች ዙሪያ እንዲወያዩ የተጠራ ስብሰባ ነበር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ኢጋድ አባል ሀገራቱን ስብሰባ እንዲጠራ ኢትዮጵያ ጥያቄ ማቅረቧን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ከፍተኛ ውጥረት የፈጠረው የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ሰነድ ከተፈረመ፣ ዛሬ አንድ ወር ሞልቶታል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ውጥረቱ አካባቢያዊ መፍትሔ እንዲያገኝ እንደምትሻ፣ ዛሬ ኀሙስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ያስታወቁት ቃል አቀባዩ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤትም መሰል አቋም ማንጸባረቁን ገልጸዋል፡፡

በጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ስላራመደችው አቋምም ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG