በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መለስ በቅርቡ እንደሚመለሱ አቶ ስብሃት ነጋ አስታወቁ፤ የበጀት አስፀዳደቁ ትክክል አይደለም ሲሉ እንደራሴ ግርማ ሠይፉ ነቀፉ


ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ

በውጭ ሃገር በሕክምና ላይ ናቸው የተባሉት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጤንነት ሁኔታ አስጊ እንዳልሆነና በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥም ወደሥራቸው እንደሚመለሱ ከሕወሓት መሥራቶችና አንጋፋ መሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ስብሃት ነጋ ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የት እንደሚገኙና የሕመማቸውም ዓይነት ምን እንደሆነ ለመናገር ያልፈለጉት አቶ ስብሃት ነጋ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ከመስጠት ይልቅ ምናልባት ከአሥር ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሥራቸው ላይ ሆነው እንደሚታዩ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡



በአሁኑ ጊዜም እርሣቸው በሌሉበት ሁኔታ የእርሣቸውን ሥራ እየሠራ ያለው ማን እንደሆነ ሲናገሩ “ክልሎች የየራሣቸው ምክር ቤቶችና የሥራ አስፈፃሚ አካላት ያሏቸው በመሆኑ፣ ሥልጣኑም ከክልል ወደ ማዕከል የሚወጣ በመሆኑ ሕዝቡ እራሱን እያስተዳደረ ነው” ብለዋል፡፡ በመሆኑም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አለመኖር የሚያስከትለው የጎላ ተፅዕኖ እንደማይኖር አመልክተዋል፡፡

በፌደራል ደረጃም የሚያስተባብራቸው ፓርላማ ያላቸው በመሆኑ ፓርላማው አሸናፊው ፓርቲ በሚያቀርብለት መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ምክትሉን አፅድቆ የሚተዳደር በመሆኑ መለስም ሆኑ ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢመጣ ሰው እንጂ ተቋም አለመሆኑን፤ ተቋም የሆነው ፓርላማ ግን ሥራውን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

“አሁን ክፍት ቦታ የለም” ብለዋል አቶ ስብሃት፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ካቢኔው ሥራቸውን እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመው “ሥልጣንና ኃላፊነት የተሰጠው አካል የለም ካለም ደግሞ ፓርላማው ይመርጣል” ብለዋል፡፡ በመሆኑም የሥልጣን ሽኩቻም ሆነ ትግል የሚፈጠርበት ምክንያት እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የፓርላማው የዘንድሮው ዓመት አዘጋግ እና የበጀቱም አስፀዳደቅ ከተለመደው ውጭ እንደሆነ በፓርላማው ውስጥ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ ተናግረዋል፡፡



ሪፖርቱንና ከአቶ ስብሃት ነጋ እና ከአቶ ግርማ ሠይፉ ጋር የተደረጉትን ቃለ ምልልሶች ሙሉ ቃሎች ከተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡ የድምፅ ፋይሎቹ በዚህ ገፅ የላይኛው የቀኝ ጫፍ ላይ ከፅሁፉ መጀመሪያ አጠገብ ይገኛሉ፡፡ ለማዳመጥ MP3 የሚሉትን ይጫኑ

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )


XS
SM
MD
LG