በኢትዮጵያ፣ በርካታ ብዙኀን መገናኛዎች፣ ከማስታወቂያ ገቢ ዕጦት በመነጨ የገንዘብ ዐቅም ማነስ ምክንያት እየተዘጉ መኾናቸውን ባለሞያዎች አስታወቁ፡፡
ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የዘርፉ ተዋናዮች፣ የማስታወቂያ ገቢ ለማግኘት አለመቻል ለቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና የኅትመት ውጤቶች መዘጋት ምክንያት እየኾነ እንዳለ አመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት በበኩሉ፣ በተጠቀሰው ችግር ምክንያት ከገበያ የወጡ የኅትመት ውጤቶች እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች መኖራቸውን አረጋግጦ የጉዳዩን አሳሳቢነት ገልጿል። ችግሩንም ለመፍታት ያስችላል ያለው የሚዲያ ፈንድ እንዲቋቋም፣ “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቄያለኹ፤” ብሏል፡፡
መድረክ / ፎረም