ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
ዋሽንግተን ዲ.ሲ ወደሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ትናንት ሐሙስ፣ ታኅሣስ 3/2006 ዓ.ም የሄዱ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ የዛሬ ሃምሣ ዓመት ለኔልሰን ማንዴላ የሰጠቻችውን ፓስፖርት የኮምፕዩተር ቅጂ አበርክተዋል፡፡
ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ለቪኦኤ እንደገለፁት ሥጦታውን የተቀበሉት የኤምረሲው አንደኛ ፀሐፊ ኢትዮጵያ ለማንዴላ ፓስፖርት የሰጠችው ከራሣቸው ሃገር ከደቡብ አፍሪካ በፊት መሆኑን ገልፀው እዚያ ለተገሀነትና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉም ምሥጋና ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡
ኦባንግ ሜቶ ባስተላለፉት መልዕክት ማንዴላ የተዉልን ትልቁ ትምህርት ፍቅር መሆኑን አመልክተው በኢትዮጵያም ብሔራዊ እርቅ እንዲደረግ፣ በጎሣ መከፋፈልም እንዳይኖር አሳስበዋል፡፡
አቶ ኦባንግ አክለውም ልክ የዛሬ አሥር ዓመት በዛሬው ዕለት ጋምቤላ ውስጥ ብዙ ሰው መገደሉንና አሥረኛውን ዓመት እየዘከሩ መሆኑን ገልፀው ከዚያ በኋላም ኦጋዴንና ሌሎችም አካባቢዎች ላይ ጠፋ ካሉት ህይወት ትምህርት እንዲወሰድ መክረዋል፡፡
ከአቶ ኦባንግ ሜቶ ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ ‘ዴቪድ ሞትፃማዪ’ በሚል ስም ሙያው “ጋዜጠኛ” የሚል ፓስፖርት እአአ በ1962 ዓ.ም ሰጠች፡፡
ኔልሰን ማንዴላ ከእሥር ዕሁድ፣ የካቲት 4/1982 ዓ.ም ከእሥር ተፈቱ፤ ከስምንት ቀናት በኋላ፤ ሰኞ የካቲት 12/1982 ዓ.ም ሃገራቸው ደቡብ አፍሪካ የሃገራቸውን ፓስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጠቻቸው፡፡
ኔልሰን ማንዴላ ከሃያ ሰባት ዓመታት እሥር በተፈቱ በሃያ ስድስተኛውና የመጀመሪያውን የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት በያዙ በ18ኛው ቀን ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ነበር፡፡ /ሐሙስ፣ የካቲት 29/1982 ዓ.ም ገብተው ዓርብ የካቲት 30/1982 ዓ.ም ወጡ፡፡/
ስለኔልሰን ማንዴላ ፓስፖርቶች የሚናገረውን የማንዴላ ፋውንዴሽን የዌብሣይት ገፅ ለማየት ከታች ያለውን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፡፡
http://www.nelsonmandela.org/news/entry/passports-tell-a-story