በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል አምስት ወረዳዎች የተከሰተው የምግብ እጥረት ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እያስከተለ ነው


በሰሜን ወሎ ዞን በቡግና ወረዳ እና በዋግምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አራት ወረዳዎች ከፍተኛ የሆነ ምግብና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መከሰቱን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አስጠንቶታል የተባለ አንድ የዳሰሳ ጥናት አመለከተ።

የአካባቢው ባለሥልጣናት በአካባቢው ያለው የሰብአዊ ድጋፍ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የሚገኘው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በሁለቱ ዞኖች ሰሞኑን አደረኩት ባለው የዳሰሳ ጥናት በአካባቢዎቹ ባጋጠመው የምግብ እጥረት ቀውስ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

የአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ቀንድ የአማርኛው አገልግሎት ከታኅሳስ 12 እስከ ታኅሳስ 13 ድረስ በቡግና ወረዳ አራት ቀጠናዎች የተደረገውን የዳሰሳ ጥናት ግልባጭ አግኝቷል።

የዳሰሳ ጥናቱን ለማድረግ በወልደያ ዩንቨርስቲ ከተመረጡት አምስት አባላት መካከል አንዱ እንደኾኑና የጥናቱ ቡድን መሪ መኾናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት አቶ ጌታነው ሰውነት ከተመረጡ የከአካባቢው ነዋሪ ጋራ ባደረጉት ውይይት የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን እንደሰሙ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል አምስት ወረዳዎች የተከሰተው የምግብ እጥረት ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እያስከተለ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:21 0:00

ስለ ዳሰሳ ጥናቱ የተጠየቁት የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነር አቶ ተስፋው ባታብል ፣ "በቡግና ወረዳ የተመጣጠነ የምግብ ችግር መኖሩ የታወቀ ነው። ይህንን መሰረት በማድረግ የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ስፍራው እየላክን ነው።" ብለዋል። እየተደረገ ባለው ድጋፍም ህፃናቱ በማገገም ላይ መኾናቸውን ገልጸው፣ "በወልደያ ዩንቨርስቲ የተደረገው ጥናት የጋራ እውቅና የለውም። የጋራ መገምገሚያ ነጥብ ተይዞ የታየ አይደለም። ወደ ፊት የሚታይ ይሆናል። አሁን ግን በመንግሥት በኩል ዕውቅና የለውም። እንደዚኽ ዐይነት ችግር ሲገጥም ሰው ሊሞት ይችላል ይህ ደግሞ በጥናት መረጋገጥ አለበት። ስለዚህ ዩንቨርስቲው ያጠናው ጥናት የጋራ ያልኾነና ከመንግሥት እውቅና ውጭ ነው" ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG